Jan
የጠበቆቹ የኳስ ቡድን
በአገራችን የሥራ ባህል ውስጥ መሮጥ እና መድከም የውጤታማነት መለኪያ ተደርገው ይወሰዳሉ። በተለይ እኛ የሕግ ባለሙያዎች፣ የሰዎችን መብት ለማስከበርና ፍትህን ለማስፈን ስንባዝን፣ ትልቁን የፍትህ መሳሪያችን የሆነወን የራስ ደህንነትና ጤናን እንረሳዋለን። አብዛኛው ጠበቃ ለሊት ሰነዶች ሲያገላብጥ ቆይቶ ፣ ጠዋትና ቀን ችሎት ቆሞ ተከራክሮ በመሃል ባለው ሰዐት መዝገብ ላይ ሲሰራ ይቆያል። ከዛም ምሽት ላይ በድካም ዝሎ ወደ ቤት

