Jan
በአገራችን የሥራ ባህል ውስጥ መሮጥ እና መድከም የውጤታማነት መለኪያ ተደርገው ይወሰዳሉ። በተለይ እኛ የሕግ ባለሙያዎች፣ የሰዎችን መብት ለማስከበርና ፍትህን ለማስፈን ስንባዝን፣ ትልቁን የፍትህ መሳሪያችን የሆነወን የራስ ደህንነትና ጤናን እንረሳዋለን።
አብዛኛው ጠበቃ ለሊት ሰነዶች ሲያገላብጥ ቆይቶ ፣ ጠዋትና ቀን ችሎት ቆሞ ተከራክሮ በመሃል ባለው ሰዐት መዝገብ ላይ ሲሰራ ይቆያል። ከዛም ምሽት ላይ በድካም ዝሎ ወደ ቤት ይገባል። ይህ ኑሮን ለማሸነፍና ኃላፊነትን ለመወጣት የግድ ነው ብለን የምናስበው የሥራ ጫና ፣ ቀስ በቀስ በአካላዊና በአእምሯዊ ጤንነታችን ላይ ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለን ይገኛል።
ይህንን ክፍተት ለመሙላት የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች የጤና ስፖርት ማህበር ላለፉት ጥቂት ወራት እያከናወነ ያለው ተግባር ለሁላችንም አርአያ የሚሆን ነው። ማህበሩ ስፖርትን የባለሙያዎች የአኗኗር ዘይቤ ጤናማ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ትልቅ ለውጥ እያመጣ ይገኛል፡
1 .ባለሙያዎች ከቢሮ ወጥተው ለራሳቸው ጊዜ እንዲሰጡና መንፈሳቸውን እንዲያድሱ አግዟል።
2. በችሎት ውስጥ የነበረውን የክርክር መንፈስ፣ በሜዳ ላይ ወደ ትብብርና ወንድማማችነት ቀይሮታል።
3. የስፖርት ማህበሩ ባለሙያዎች ከሥራ ውጭ እንዲገናኙ፣ ሃሳብ እንዲለዋወጡና በሥራቸውም ላይ ይበልጥ እንዲናበቡ በማድረግ የፍትህ ሥርዓቱን ጥራት እያሳደገው ነው።
የጤና ስፖርት ማህበሩ እያከናወነ ያለውን የሚያስመሰግን እንቅስቃሴና ባለሙያዎችን እንዴት እያስተሳሰረ እንደሆነ ይበልጥ ለማወቅ ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ፡

